Lottery Results
Coming soon..
Messages




Latest
News
Stay up-to-date with the latest news, announcements,
and insights from ethiopian lottery service.

አስረሳኸኝ ጌታቸው ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም በወጣው የዕንቁጣጣሽ ሎተሪ የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆኗል፡፡
አስረሳኸኝ ጎረቤቶቹን ጠርቶ በዓሉን ቢያደምቅም በዚያን ሰአት በሙሉ ልቡ ከነሱ ጋር እንዳልነበረ ይናገራል፡፡ የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ በዋዜማው ጳጉሜ 5 ስለወጣና እድሉን ለማወቅ ጓጉቶ ስለነበር የገዛቸውን የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ትኬቶች ከኪሱ አውጥቶ ከደራው ጨዋታ ገለል አለ፡፡ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎትን የቴሌግራም ገጽ ከፍቶ የዕጣ ማውጫውን ሲመለከት የአንደኛው ዕጣ ቁጥር 0103072 ደምቃ ታየችው፡፡ ማመን ስላልቻለ ደጋግሞ አየ፡፡ የ1ኛው ዕጣ የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ መሆኑን ደጋግሞ አረጋገጠ፡፡ በተደበላለቀ ስሜት ሆኖ የሞቀ ጨዋታ ይዘው የነበሩትን ጎረቤቶቹን የምስራች አለኝ፣የ20 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆኛለሁ ቢልም የቀልድ ስለመሰላቸው የምስራቹን ከቁም ነገር የቆጠረው አልነበረም፡፡

ወጣት ማቴዎስ መንዲዳ በቶምቦላ ሎተሪ በ4ኛ ዕጣ ተሸላሚ
የአዲስ አበባ ነዋሪው ወጣት ማቴዎስ መንዲዳ የቶምቦላ ሎተሪ የአራተኛ ዕጣ ዕድለኛ ሲሆን ሽልማቱን ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተረክበዋል ፡፡ ወጣት ማቲዎስ የረጅም ጊዜ የሎተሪ ደንበኛ በመሆኔ ከብዙ ሙከራዎች በኋላ ሎተሪ ዛሬ ዕድለኛ አድርጎኝ ፈጣሪ ይመስገን የደስታየ ምንጭ ሆነዋል በማለት ገልጸዋል ፡፡

የከንባታ ዱራሜ ከተማ ነዋሪው ገነቱ ታምራት
ገነቱ ታምራት የተወለደው በከምባታ ዱራሜ ከተማ ነው፡፡ በትምህርቱ በችግር ምክንያት ከስምንተኛ ክፍል ማለፍ አልቻለም፡፡ ትምህርቱን አቋርጦ ሊስትሮ ሆነ፤ ከዚያም እዚያው ዱራሜ ከተማ የጎሚስታ ስራ ጀመረ፡፡ ዱራሜ አልሆንልህ ሲለው ሀዋሳ ገብቶ ጎሚስታ ስራውን ቀጠለ፡፡ ጎሚስታ ስራውን ትቶ ደግሞ የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ረዳት ሆነ፡፡ሚስትም አገባ፡፡ ብዙም ሳይቆይ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ የሲኖትራክ ሹፌር ሆነ፡፡ አሁን የአንድ ልጅ አባት ነው፡፡ ከሊስትሮ ስራው ጀምሮ ሎተሪ ያለማቋረጥ የሚቆርጠው ገነቱ በሀዋሳ ከተማ ከስራው አረፍ ብሎ ቡና እየጠጣ የቆረጣት የልዮ ዕድል ሎተሪ የ2ኛ ዕጣ የ5 ሚሊዮን ብር አሸናፊ አድርጋዋለች፡፡
ሚሊዮን ሎተሪ ይቁረጡ

Ethiopian Lottery Service (ELS)
Ethiopian Lottery Service (ELS) was established as the first autonomous and legal state lottery by Proclamation number 183 in 1954EC. It was established with the purpose of generating revenue through undertaking lottery activities. The proclamation was enacted in 1954EC to govern gaming and gambling making lottery a legitimate activity with government monopoly.
As of January 2007, the Government of Ethiopia wanted to involve the private sector in the area of Lottery on the basis of the market-oriented economic policy of the government. Accordingly, ELS Re-establishment Proclamation No.510/2007 was granted to ELS to carry out lottery activities alongside issuing license and regulating the conduct of lottery activities practiced by the private sector.
Contact
Call Us
0111550144 / 0111550144
Fax
0111267323 / 0111267323
Find Us
Dej. jote St, 1165
Addis Ababa, Ethiopia